ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  በገጠር ኢነርጂ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና እና የፈጠራ ስራ ባለቤቶችን በሚከተሉት ዘርፎች ላይ አወዳድሮ መሸለም ይፈልጋል፡፡

ከነዚህም

በፀሃይ የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ፣ በተሻሻለ የማብሰያ ምድጃ የገጠር ኢነርጂ ፣.በነዳጅ የገጠር ኢነርጂ፣ በንፋስ ሃይል የገጠር ኢነርጂ፣ በባዮጋዝ የገጠር ኢነርጂ እና በሌሎች የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማራችሁ  ኢንተርፕራይዞችና የፈጠራ ስራ ባለቤቶች ከመጋቢት 04 ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 2012 ዓ.ም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

  ማሳሰቢያ፡-

ተወዳዳሪዎች የማወዳዳሪያ ቅፅ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዌብሳይት  WWW.MINT.gov.et/competition call በማውረድና በመሙላት ወደ ኢሜል አድራሻችን innovation.resarch@mint.gov.et በመላክ መወዳደር ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችን  WWW.MINT.gov.et  ወይም በፌስቡክ አድራሻችን  Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia ማግኘት ይችላሉ፡፡ አልያም በስልክ ቁጥር 0911661675 ወይም 0912612679 ይደውሉ፡፡

          የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር