News News

​በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአንስሳት ሃብት ልማት በሶማሌ ክልል ተጀመረ፡፡

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአንስሳት ሃብት ልማት በሶማሌ ክልል ተጀመረ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የሶማሌ ክልል መንግስትና የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን ነው ፕሮጀክቱን ያስጀመሩት፡፡
የእንስሳት ሃብት ልማቱ በተለይም በወተት ምርት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን የእንስሳት መኖ ዝግጅትን እና ህክምናንም ያካተተ ነው፡፡
ፕሮጀክቱን ተፈፃሚ ለማድረግ ለአርብቶ አደሮች ስልጠና እንደሚሰጥና የመኖ ዘር እንደሚከፋፈልም ተጠቁሟል፡፡
3 የእንስሳት የህክምና ጣቢያዎችም ይከፈታሉ፡፡
በእንስሳት ህብት ከአፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ኢትዮጵያ ከሃብቷ እየተጠቀመች አይደለችም ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር ፕሮጀክቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል፡፡
ከራስ ጥቅም አልፎ ለጎረቤት ሀገራት ለመላክ የሚያስችል አቅም ለመፍጠርም እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡
ፕሮጀክቱን በማስጀመሪያ ዝግጅት ላይ የተገኙት የአካባቢው አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፕሮጀክቱ በክልሉ በመጀመሩ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

Archive news Archive news