News News

​በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመራና ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ የቢዝነስ ልኡካን የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን በኢትዮጵያ የመገንባት እቅድ እንዳላቸው ተናገሩ ፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመራና ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ የቢዝነስ ልኡካን የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን በኢትዮጵያ የመገንባት እቅድ እንዳላቸው ተናገሩ ፡፡
የቢዝነስ ልኡካኑ የህክምና መሳሪያዎችን እና መድሃኒቶችንም በኢትዮጵያ ለማምረት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በህክምና ዘርፍ ጥቅም ላይ በማዋል የሚጀምር ሲሆን ወደ ሌሎች ዘርፎችም ለማሸጋገር ነው የታቀደው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሲሳይ ቶላ በኢትዮጵያ በሚያርጉት የንግድ እንቅስቃሴ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልፀውላቸዋል፡፡
ልኡካኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የጎበኙ ሲሆን ሚኒስትር ዴኤታው የተቋሙን እንቅስቃሴ የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል፡፡

Archive news Archive news