News
የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ተጠናቆ ይፋ ተደረገ።
የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲው ፀድቆ ወደ ስራ ከገባ 8 አመታትን ያስቀጠረ ሲሆን በዘርፉ የተማረ ሰው ከማፍራት ጀምሮ በርካታ አላማዎቹን ማሳካት ቢችልም ክፍተቶችም ነበሩበት፡፡
የተሰራዉ ክለሳ ስራ ፈጠራን ማዕከል በማድረግ የነበረውን ክፍተት ማሟላት የሚችል ነው ተብሏል ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ.ር ኢንጂ) የፖሊሲ ክለሳው በሳይንስና ኢንጅነሪንግ ዘርፍ የተመረቁ ወጣቶች ወደ ኢንዳስትሪውና አገልግሎት ዘርፉ ለማስተሳሰር የፖሊሲ አቅጣጫ ስለሚያስፈልግ፣ዲጅታል ኢኮኖሚውን የመገንባት ሒደት በፖሊሲው ተደራሽ ማድረግ እንዲቻል ፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መስራችና መሪ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ለገበያው በዋጋና ጥራት ተወዳዳሪ ምርቶችን ማምረት የሚችሉ ኢንዳስትሪዎች ለመገንባ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ነው ብለዋል።
መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራ ተርታ ለመሰለፍ የሚደርገው ጉዞ መሪ ሞተር ቴክኖሎጂ እንዲሆን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ቴክኖሎጅ በባህሪው ፈጣን ለውጥ ስላለው ክለሳውን ማካሄዱ የግድ ሆኗል ብለዋል።
በፖሊሲው ክለሳ ሂደቱ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ በማዘጋጀት የተካተቱ ሲሆን በቴክኖሎጂ ዙርያ የተሰማሩ ተቋማትና ቴክኖሎጂን በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙ አካላት ተወካዮችና የዘርፋ ተመራማሪዎች ሲሳተፉበት ቆይተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የንግድና ዴቨሎፕመንት ኮንፈረንስ (UNCTAD) የቴክኖሎጂና ሎጂሰቴክስ ዳይሬክተሯ ሻሚክ ሲሪማን ኢትዮጲያ የኢኮኖሚ ለውጧን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የጀመረቸውን እንቅስቃሴ በማድነቅ የተከለሰውን የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ወደ ተግባር በማስገባት በዘርፉ የሚጠበቀውን ለውጥ እንዲመጣ ተስፋ የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡
Archive news
-
ዓለም አቀፍ የባሉት ግብይት (Electronic World Trade Platform) በኢትዮጵያ ለመጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ፡፡
-
የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ተጠናቆ ይፋ ተደረገ።
-
ሰበር ዜና
-
የወረዳ የትሥሥር መረብን (Woreda Net) አቅም ለማሻሻል እየተሰራ ነው፡፡
-
በባህር ዳር ከተማ የተገነባው የሳይንስ ካፌ ተመረቀ።
-
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል የዘረጋውን ዘመናዊ የህክምና አስተዳደር ስርዓት አስመርቆ አስረከበ፡፡
-
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማሸነፋቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንኳን ደስ አለዎት ማለት ይፈልጋል፡፡
-
የውድድር ማስታወቂያ
-
5ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ይሁኑ:-
-
መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ያደረገው ‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› የተሰኘ ድርጅት በስዊዘርላንድ ‹‹ስታንዳርድ›› የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል በኢትዮጵያ የመገንባት እቅድ እንዳለው ይፋ አደረገ፡፡
-
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የሚመራ የልዑካን ቡድን በኦስትሪያ ቬይና እየተካሄደ ባለው 63ተኛው የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አመታዊ ስብሰባ ላይ ሀገራችንን ወክሎ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
-
በቴክኖሎጂ የተደገፈ የእንስሳት ሀብት ልማት ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ተጀመረ።
-
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመራና ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ የቢዝነስ ልኡካን የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን በኢትዮጵያ የመገንባት እቅድ እንዳላቸው ተናገሩ ፡፡
-
‹‹እንጦጦ ፌሎሺፕ›› ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሶፍትዌር ማበልፀግ እና በስራ ፈጠራ ያሰለጠናቸውን ሴቶች አስመረቀ፡፡
-
በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአንስሳት ሃብት ልማት በሶማሌ ክልል ተጀመረ፡፡
-
የአፍሪካ የበይነመረብ ነፃነት መድረክ (Forum on Internet Freedom in Africa) በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው፡፡
-
በኢኖቬሽን ሳምንት ላይ የአጭር ቪዲዮ ውድድር አሸናፊዎች የዱባይ ደርሶ መልስ ትኬታውን ተረከቡ፡፡
-
ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም 3ሚሊየን የስራ እድል ለመፍጠር በያዘችው እቅድ ውስጥ የቴክኖሎጂ የስራ እድል ፈጠራ ትልቁን ድርሻ እንዲይዝ እየተሰራ ነው።
-
ካናዳ የሴቶችን ጫና በሚያቃልሉ ቴክኖሎጂ ዝርጋታ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ስራ እደግፋለሁ አለች፡፡
-
አወስትራሊያ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታን የመፍጠር እንቅስቃሴን እደግፋለሁ አለች፡፡