News News

የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ተጠናቆ ይፋ ተደረገ።

የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲው ፀድቆ ወደ ስራ ከገባ 8 አመታትን ያስቀጠረ ሲሆን በዘርፉ የተማረ ሰው ከማፍራት ጀምሮ በርካታ አላማዎቹን ማሳካት ቢችልም ክፍተቶችም ነበሩበት፡፡
የተሰራዉ ክለሳ ስራ ፈጠራን ማዕከል በማድረግ የነበረውን ክፍተት ማሟላት የሚችል ነው ተብሏል
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (. ኢንጂ) የፖሊሲ ክለሳው በሳይንስና ኢንጅነሪንግ ዘርፍ የተመረቁ ወጣቶች ወደ ኢንዳስትሪውና አገልግሎት ዘርፉ ለማስተሳሰር የፖሊሲ አቅጣጫ ስለሚያስፈልግ፣ዲጅታል ኢኮኖሚውን የመገንባት ሒደት በፖሊሲው ተደራሽ ማድረግ እንዲቻል ፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መስራችና መሪ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ለገበያው በዋጋና ጥራት ተወዳዳሪ ምርቶችን ማምረት የሚችሉ ኢንዳስትሪዎች ለመገንባ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ነው ብለዋል።
መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራ ተርታ ለመሰለፍ የሚደርገው ጉዞ መሪ ሞተር ቴክኖሎጂ እንዲሆን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ቴክኖሎጅ በባህሪው ፈጣን ለውጥ ስላለው ክለሳውን ማካሄዱ የግድ ሆኗል ብለዋል።


በፖሊሲው ክለሳ ሂደቱ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ በማዘጋጀት የተካተቱ ሲሆን በቴክኖሎጂ ዙርያ የተሰማሩ ተቋማትና ቴክኖሎጂን በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙ አካላት ተወካዮችና የዘርፋ ተመራማሪዎች ሲሳተፉበት ቆይተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የንግድና ዴቨሎፕመንት ኮንፈረንስ (UNCTAD) የቴክኖሎጂና ሎጂሰቴክስ ዳይሬክተሯ ሻሚክ ሲሪማን ኢትዮጲያ የኢኮኖሚ ለውጧን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የጀመረቸውን እንቅስቃሴ በማድነቅ የተከለሰውን የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ወደ ተግባር በማስገባት በዘርፉ የሚጠበቀውን ለውጥ እንዲመጣ ተስፋ የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡


Archive news Archive news