News News

ቅድሚያ ትኩረት ለሚሹ ተግባራት ትኩረት በመስጠት መስራት አለብን አብርሃም በላይ (ዶ.ር)የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፦

ሚኒስትሩ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ በ2012 ዓ.ም የታቀዱ፣በሂደት ላይ ያሉና የተከናዎኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርበውላቸዋል።

የተለያዩ ተቋማት የመንግስት ኢ-ሜይል አገልግሎት ፣የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት ፣ለፌደራል ተቋማትና በክልሎች ለሚገኙ የወረዳ ጽፈት ቤቶች የተሰጠ የወረዳኔት ድጋፍ አገልግሎቶች፣ የሀገሪቱን አጠቃላይ የግዦ ስርአት ዲጅታላይዝ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች፣ ስራ ማስጀመርን ለማሳለጥ (Ease of doing business) የሚያግዝ ሲስተም እና ሌሎች የስራ አንቅስቃሴዎች ያሉበት ደረጃ በሪፖርቱ ቀርቧል።

በ2025 ኢትዮጵያን በዲጅታል አለም የተሻለች ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጅ ያለበት ደረጃ እንዲሁም በሁሉም ተግባራት የስራ አንቅስቃሴ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች በሪፖርቱ ቀርበውላቸዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶር) የበለጠ ቅድሚያ ትኩረት ለሚሹ ተግባራት ትኩረት በመስጠት አንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።


Archive news Archive news