News News

Back

የኢትዮጵያ ልዩ ተውህቦ እና ተሰጥኦ ማዕከል በ2013 ዓ.ም ወደ ስራ ይገባል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች የኢትዮጵያ ልዩ ተውህቦ እና ተሰጥኦ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታዎች ዶክተር አህመዲን ሙሀመድ እና አቶ ሲሳይ ቶላ እንዲሁም የቡራዩ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይሉ ዲራርሳ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊች ተገኝተዋል።

በቡራዩ በመገንባት ላይ ያለው የኢትዮጵያ የልዩ ተውህቦ እና ተሰጥኦ ትምህርት ቤትን የግንባታ አፈጻጸም 73% ላይ የደረሰ ሲሆን የግንባታ ሂደቱን በማፈጠን እስከ ሰኔ 30 እንዲጠናቀቅና በቀጣዩ አመት ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ተቋሙ ወደ ስራ ሲገባ በቴክኖሎጂ ለማደራጀት የሚያስችሉ ስራዎች እና ከካሪኩለም ቀረጻ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ተግባራቶች በመሰራት ላይ ናቸው

በተጨማሪም ማዕከሉን ወደ ዋናው መንገድ ለማገናኘት የሚያስችል 1.4km የአስፓልት መንገድ ለመገንባትም ከከተማ እስተዳደሩ ጋር ስምምነት ላይም ተደርሷል።


News Archive News Archive