News News

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከ3 ሚሊየን በላይ ማጣቀሻ መፅሐፍትን ‹‹ኦንላይን›› ማደራጀት ችሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (/ ኢንጂ.) እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች የኢንስቲቲዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡ኢኒስቲቲዩቱ የተሽከርካሪ የአስተዳደር ስርዓት፣ የተቋማት የኢሜል መጠቀሚያ፣ የሰራተኞች መታወቂያና ባጅ አስተዳደር ሰርዓት፣ የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት፣ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር ስርዓት እና ሌሎች ስርዓቶችንና መተግበሪያዎችን መዘርጋቱንና ማበልፀጉን አስታውቋል፡፡


3ሚሊየን 37 443 ማጣቀሻዎችን (የባለቤትነት መብት የተሰጣቸው መረጃዎች፣ የህግ ጉዳዮች፣ የከፍተኛ ትምህርት እና ሌሎች መረጃዎችን ያካተተ) ‹‹በኦንላይን›› ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዱካን ደበበ ተናግረዋል፡፡
የብሄራዊ የኢኖቬሽን መረጃም ተጠንቶ መጠናቀቁና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የገለፁ ሲሆን በተቋሙ ውስጥ ሊፈቱ ይገባቸዋል ያሏቸውን ጉዳዮችም አንስተዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (/ ኢንጂ.) የተነሱ ችግሮችን በፍጥነት በመፍታትና ምቹ የስራ አካበቢን በመፍጠር ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲወጣ ለማድረግ አድንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡


Archive news Archive news