News News

​ዓለም አቀፍ የባሉት ግብይት (Electronic World Trade Platform) በኢትዮጵያ ለመጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ፡፡

ዓለም አቀፍ የባሉት ግብይት (Electronic World Trade Platform) በኢትዮጵያ ለመጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ፡፡
ግብይቱን በኢትዮጵያ ማስጀመር የሚያስችሉ ሦስት የተለያዩ ስምምነቶች ተፈርመዋል፡፡
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ከአሊባባ የቴክኖሎጂ ግሩፕ ኃላፊዎች ጋር ተፈራርመውታል።
ስምምነቶቹ ዓለም አቀፍ የባሉት ግብይት ማስጀመር፣ የአቅም ግንባታና ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
በስምምነቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢንጂ.) ፣ የአሊባባ ቡድን መስራች ቻከ ማ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምሳደር ታን ጂያን እና የተለያዩ እንግዶች ተግኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ሀገራት ውስጥ ከአምስቱ ተርታ ለመሰለፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ትኩረት ሰጥታ አየሰራች መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአሊባባ መስራችና ባለቤት ጃክ ማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሰጠችው ትኩረት፥ ወደ ኢትዮጵ እንዲመጡ እንዳደረጋቸው ተናግረዋው  ግብይቱ ኢትዮጵያ የምታመርታቸውን ምርቶች በድርጅታቸው በኩል አለም አቀፍ ግብይት እንድትፈፅም ያስችላታል ብለዋል፡፡
ጃክ ማ በአፍሪካ በዘርፉ ለሚሰማሩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችና ሴቶችን ለማበረታታት አሊባባ የቴክኖሎጂ  ቡድንና ጃክ ማ ፋዴንደሽን እስከ 100ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
 
 

Archive news Archive news