የኢ... ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 10 የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሀገር አቀፍ ሽልማት የላቁ የምርምርና የፈጠራ ውጤቶችን ለማወዳደርና ለመሸለም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ስለሆነም በግል ወይም በቡድን ወይም በተቋም የተሰራ ችግር ፈቺ የምርምርና የፈጠራ ውጤት ያላችሁ ተመራማሪዎች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች እና ተቋማት የሽልማት መመሪያዎችና የማመልከቻ ቅፆች በሚጠይቁት መስፈርት መሰረት ከተቋም/ከድርጅት/ከዩኒቨርሲቲ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ የድጋፍ ደብዳቤ እና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2012 . ድረስ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል፡፡

የፈጠራ ስራ ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ግዴታዎች

 1. ቋሚ መኖሪያው/ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነና ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው/ያላት፤
 2. የፈጠራ ስራው በመንግስት የትኩረት አቅጣጫ በሆኑት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች
 3. የሚካተት፤
 4. የፈጠራ ስራ ባለሙያዎችና ተቋማት ግኝታቸውን በተመለከተ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
 5. የፈጠራ ስራው በጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ ችግር ፈቺ ስለመሆኑ ከተጠቃሚ  ድርጅቶች/ተቋማት የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
 6. ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በመጠቀም ለውጥ ያመጣ/ች
 7. የፈጠራ ስራዎቹ በተጨባጭ የህብረተሰቡን ችግር ሊፈቱ ወይም የፈቱ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡   

የግል ወይም የቡድን ተወዳዳሪ ተመራማሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ግዴታዎች

 1. ቋሚ መኖሪያው/ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነና ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው/ያላት፣ ወይም
 2. ውጤቱ በቡድን ከተሰራ የቡድኑ አባላት መኖሪያቸው ኢትዮጵያ ውስጥ  የሆነ እና ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው፣
 3. የሚወዳደርበት/የምትወዳደርበት የምርምር ውጤት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሆነ፣
 4. የምርምር ውጤቱ ለተጠቃሚው የተሠራጨና ጥቅም ላይ የዋለ፣
 5. የምርምር ውጤቱ በጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ ችግር ፈቺ ስለመሆኑ ከተጠቃሚዎችና ድርጅቶች/ተቋማት የማረጋገጫ ደብዳቤ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣
 6. የምርምር ውጤቱ ከዚህ በፊት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገር አቀፍ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሽልማት ያልተሸለመ፣
 7. የምርምር ውጤቱ የሀገራችንን የወቅቱን የቴክኖሎጂ ፍላጎት ክፍተት የሚሞላ፣

 

 1. ተወዳዳሪዎች ስለ ምርምሩ አካሄድና ውጤት ማለትም፡- 
 • የሚፈታው ችግር (Statement of the Problem)
 • ለማከናወን  የተጠቀሙበት ዘዴ፣
 • ወሰን፣
 • የተገኘው ዕውቀት/ቴክኖሎጂ
 • ዕውቀት/ቴክኖሎጂ ከዚህ በፊት ከነበረው ቴክኖሎጂ ጋር ሲነጻጸር ያለው ጠቀሜታን በማካተት አጭር የፅሁፍ መግለጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተወዳዳሪ ተመራማሪዎች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች እና ተቋማት የሽልማት መመሪያዎች፣ የማመልከቻ ቅፃቅፆች ቸርችል ጎዳና ሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት ጀርባ ከሚገኘው /ቤታችን በአካል በመምጣት ወይም ከዌብ ሳይታችን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲዎች/ቢሮዎች የላቁ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ሞዴሎች የሰሩ የመጀመሪያ ዲግሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች፣ የሳይንስና የሂሳብ ተማሪዎችንና መምህራንን እንዲሁም ሰልጣኝና አሰልጣኞችን በተላከላችሁ የሽልማት መመሪያዎችና ቅፆች መሰረት አወዳድራችሁ እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡

ለዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 0932182940 ወይም የመስሪያ ቤቱን ዌብ ሳይት http://www.mint.gov.et/competition-call  መመልከት ይቻላል፡፡

                        ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር