‹‹ወደ አዲስ ጉዞ›› በሚል በዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት አዘጋጅነት ላለፈው አንድ አመት ሲካሄድ የነበረው የመጀመሪያ ምዕራፍ ጉባኤ ማጠቃለያ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል ለግሉ ዘርፍ ክፍት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ፈጣን የበይነመረብ ግንኙነት ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ ኢትዮጵያ እየሰራች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ አካታች የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እያደረገች መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቷ ተወዳዳሪ የሆነ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገናኘ እና አካታች የሆነ የበይነ መረብ ግንኙነት መዘርጋት በቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ያለ ማሻሻያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው በማደረግ ላይ ያሉ ሀገራት የበይነመረብ ግንኙነትንና የዲጂታል ትራንስርሜሽንን ለማጠናከር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻችን ለማገናኘት፣ አይ ሲ ቲን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን መሰጠት እና አካታች የሆነ የበይነ መረብ ግንኙነትን መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡