ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኢትዮጵያ በቀጣይ አመት የምታዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤን እደግፋለሁ አለ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ከሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ቻርለስ ዲንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኢትዮጵያ በቀጣይ አመት የምታዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በገንዘብና በቴክኒክ እንደሚደገፍ ምክትል ስራ አስፃሚው ቻርለስ ዲንግ ተናግረዋል። በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍም ከመንግስትንና ከግሉን ዘርፍ ጋር በጋራ መስራት እንደሚፈልጉም ጠቁመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ሁዋዌ አለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ዝግጅትን ለመደገፍ ቃል በመግባቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ግሩፕ በዓለም ላይ ካሉት ሰራተኞቹ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በጣም ጥቂት ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ላይ በትኩረት እንዲሰራም ጠይቀዋል።

ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ግሩፖ በዓለም ላይ ከ197ሺ በላይ ሰራተኞች አሉት። አፍሪካ ውስጥ ካሉት 8ሺ 600 ሰራተኞች ውስጥ 76 ከመቶ አፍሪካውያን ሲሆኑ ኢትዮጵያውያ ውስጥ ካሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ሰራተኞች ውስጥ 80 ከመቶዎቹ የሀገር ውስጥ ሰራተኞች ናቸው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook