ህዋዌ ከመሰረት ልማት ግንባታ ባሻገር የእውቀት ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

ህዋዌ ቴክኖሎጂ የ2022 የኢትዮጵያ አጋርነት ሰብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ህዋዌ ከመሰረት ልማት ግንባታ ባሻገር የእውቀት ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የእውቀት ሽግግሩ የአገር ውስጥ ተቋማት ዲጂታል የንግድ ስርዓቶችን እንዲረዱና የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲያሳኩ ያግዛል ብለዋል።

የህዋዌ ኢትዮጵያ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኮዊን ካኦ ህዋዌ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ከ158 የሀገር ውስጥ አጋሮች ጋር የሚሰራ ሲሆን ለ3ሺ 700 ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

ህዋዌ በኢትዮጵያ፣ ለኢትዮጵያ በሚል እየሰራ መሆኑን ያብራሩት ምክትል ስራ አስፈፃሚው የስራ እድል ከተፈጠራላቸው ውስጥ 70 ከመቶዎቹ የሀገር ውሳጥ ዜጎች ናቸው ብለዋል።

ህዋዌ በኢትዮጵያ በ23 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የዲጂታል አካዳሚ ያለው ሲሆን ተማሪዎች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በቁ እውቀት እንዲጨብጡ እያስቻለ ነው ተብሏል።

ህዋዊ ኢትዮጵያ በቀጣይ አመት የምታስተናግደውን 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ለመደግፍ ቃል መግባቱ ይታወሳል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook