ስለ እኛ

ተቋማችን

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ አንድ መሰረት አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆነው በአዲስ መልክ እንደገና ከተደራጁት 19 የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች አንዱ ሲሆን በስሩ አምስት ተጠሪ ተቋማትን ያስተባብራል፡፡

flipimage
 • ተልዕኮ
 • ራዕይ
 • እሴቶች
 • ተቋማዊ ፍልስፍና
 • ተግባራትና ኃላፊነቶች/ስለ ስራችን
 • ታሪካዊ ዳራ/አመሰራረት

የኢኖቬሽን ሥርዓት የሚተገበርበትን ከባባዊ ሁኔታን በመፍጠር የሀገሪቱን የዕድገት ቀጣይነት ማረጋገጥ

በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ሥራንና ሀብትን ለመፍጠር የምትመች ሀገር ተገንብታ ማየት

• በጎ ሕሊና እና ቅን ልቦና፣
• የማይረካ የመማር ጥማት፣
• የሥራ ፍቅርና ትጋት፣
• ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣
• ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣

 • ዕውቀት ሀብት ነው፣
 • ለአዳዲስ ሀሳቦች ዕውቅና እንሰጣለን፣
 • ትጋት የአዎንታዊ ለውጥ ሀይል ነው፣
 • ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የአዲሱ ትውልድ ቋንቋ ነው፣
 • ኢኖቬሽንን ማበረታታት ለትውልድ ተስፋን መመገብ ነው፣
 • የዘመነ ቴክኖሎጂ የዕድገታችን መሰረት ነው፡፡

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ አንድ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡
1. የአገሪቱን የልማት አቅጣጫ መሠረት ያደረገ አገራዊ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል፣ ያስፈጽማል፣ በብቃት ለማስፈጸም የሚስችል ተቋማዊ አቅም እና የሰው ኃይል ልማት ያቅዳል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
2. ለክልሎች ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት አቅም ግንባታ አስፈላጊውን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
3. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና አስተማማኝነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚስያችሉ ደረጃዎችን ይወስናል፤ ተግባራዊ መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፡፡
4. በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማትንና ባለሙያዎችን አቅም ግንባታን ይደግፋል፣ የሙያ ማህበራትንና አካዳሚዎችን ይደግፋል፣ ያበረታታል፤
5. የአገሪቱ ስርዓተ ትምህርት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት አንፃር መቃኘቱን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይተባበራል፤
6. የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለመዳሰስ፣ ተገቢ ቴክኖሎጂዎችን ለማፈላለግና በስራ ላይ ለማዋል የሚስችል ሥርዓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይዘረጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
7. ለአገሪቱ እድገት አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የጥናትና ምርምር መስኮችን ይለያል፤ አገራዊ የምርምር ፕሮግራሞችን ያስተባብራል፤
8. አገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል፣ ለማሳደግና ለገበያ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥናቶችን፣ የምርምርና ስርፀት ስራዎችን ያበረታታል፣ ወደ ተግባር እንዲገቡ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መዳበር የበለጠ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ የሚችሉ ግለሰቦችን፣ የሙያ ማህበራትንና አካዳሚዎችን ያበረታታል፣ ይደግፋል፤
9. ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማትና ለፈጠራ ሥራዎች እድገት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማትና ማበረታቻ የሚሠጥበትን ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፤
10. በየዘርፉ በሽግግር የሚመጡ ቴክኖሎጂዎችን መረጃ ይመዘግባል፣ ኮዲፋይ የማድረግና የማቀብ ስራዎችን ያስተባብራል፣ ለቀጣይ ስራ እንቅስቃሴም እንዲውሉ ያደርጋል፤
11. ለሕዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያተኮሩ መሠረታዊ ሲስተሞችና አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑና ለተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎት ሊሰጡ በሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸታቸውን ያረጋግጣል፤
12. የምርምር ሥራዎችን ለማስተባበር የሚያግዙ ምክር ቤቶችን ያቋቁማል፤ ያስተባብራል፤ ይደግፋል፤
13. የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ መረጃ ቋት ያደራጃል፣ መረጃዎችን ያጠናቅራል፣ አገራዊ የመረጃ አያያዝ ደረጃ ያወጣል፤
14. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የፌደራልና የክልል መንግስታዊ ተቋማት የመረጃ ሥርዓትን ይገነባል፣ ያቀናጃል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንፎርሜሽን መረብ የመዘርጋት ሥራን ይደግፋል፤
15. የአገሪቱን ከፍተኛ መለያ ዶሜይን ስም አገራዊ የአስተዳደር ስርዓት እንዲፈጠርና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚመለከታቸውን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ በመንግስታዊ ተቋማት የመረጃ ስርዓትን ለመገንባትና ለማቀናጀት የዶሜይን ስም ያድላል፣ አድራሻ ይመዘግባል፣ ይቆጣጠራል፤
16. የጨረራና የጨረር አመንጪ ቁሶች አጠቃቀምና አወጋገድ ቁጥጥር ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፤
17. ብሔራዊ የቴሌኮሙኒኬሽ ቁጥር ፕላን ያወጣል፣ ቁጥሮችን ይመድባል፣ ያስተዳድራል፣ አጠቃቀማቸውን ይቆጣጠራል፤
18. የቴሌኮሙኒኬሽንና የፖስታ አገልግሎቶች በመስጠት ስራ ላይ ለሚሰማሩ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጠራል፣ የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን የቴክኒክ ብቃት ያረጋግጣል፤
19. ለኢትዮጵያ የተመደበውን የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ አጠቃቀም ይፈቅዳል፣ ይቆጣጠራል፤
በስራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎችና ድንጋጌዎች ኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂን በተመለከተ ለመገናኛኛ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባራት፤ ቴክኖሎጂን በተመለከተ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተሠጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባራት በዚህ አዋጅ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተሰጥተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሚሽን ደረጃ በአዋጅ ቁጥር 62/ 1968 የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው:: በመቀጠል በ1997 ዓ.ም “የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ” በሚል እንደገና ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በድጋሚ “የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር” በመባል በሚኒስቴር ደረጃ በአዋጅ ቁጥር 603/2001 ተቋቁሟል::

በ2011 ዓ.ም የአስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ “የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር” በመባል እንዲደራጅ ተደረገ፡፡ ተቋሙ በኮሚሽን ደረጃ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በቅርብ ጊዜ በኢኖቬሽናዊ የቴክኖሎጂካል ዕውቀትና ምርምር በታገዘ ክህሎት፣ ሀገራችንን ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያሸጋግር ድልድይ ተገንብቶ ማየት የሚል ራዕይን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል፡፡

ፈጠራዎች

0 +
አዳዲስ የፈጠራ፤ የቴክኖሎጂ የጥናትና ምርምር መስኮች ተለይተው ተተገብረዋል፡፡

ሃሳቦች

0 +
ለአገሪቱ እድገት አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ ለሆኑ ሃሳቦች ድጋፍ ተደረጓል

ፕሮጀክቶች

0 +
የተደገፉ የምርምር ፕሮጀክቶች