ስኬቶች

ስኬቶች

ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ማድረግ

የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የብሔራዊ ድጅታል ስትራቴጂ መዘጋጀቱ፣

ሚኒስቴሩ የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠናን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ዲጂታል መታወቂያ ለማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል፡፡ በስርዓቱ ውስጥ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እና የፋይናንስ ስርዓትን በሙሉ አካቶ የሚይዝም ጭምር ነው፡፡

2020

ኢ-ኮሜርስ

ዓለም በኢንተርኔት ገበያ ውስጥ ከፍተኛ ገንዘብ በሚያንቀሳቅስበት በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ውስጥ በዚህ ዘርፍ እምብዛም እንቅስቃሴ አይደረግም፡፡ የኢንተርኔት ገበያውን ለመቀላቀልና የግብይት ስርዓቱን ቀልጣፋ ለማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ የምስራቅ አፍሪካ የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ለመግንባት ታቅዷል፡፡ ኢትዮጵያ የግብይቱ መተላለፊያ ኮሪደር ሆና የምታገለግል ሲሆን ስርዓቱ ወደ ስራ ሲገባ ለ100ሺዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖር ያስችላል፡፡

Nov 09, 2017

የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት

ሚኒስቴሩ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የዘረጋውን የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት አስመርቆ ለሆስፒታሉ አስረከቧል፡፡ ስርዓቱ የታካሚዎችን እንግልት በማስቀረት የሃኪሞችን ድካም ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ነው፡፡ አገልግሎቱ ሃኪሞች የታካሚዎቻቸውን መረጃ ለመፃፍ በእጅ ፅሁፍ መልክ የሚፅፉበት በሀገራችን ወጣት ባለሙያዎች ዲዛይን በተደረገ ታብሌት ታግዞ ስራ ላይ ይውላል፡፡

Nov 09, 2017

በሬን የሚተካ ዘመናዊ ማረሻ

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራውና በእጅ የሚገፋ ዘመናዊ ማረሻ በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ "በሬ ለምኔ" የሚል መጠሪያ የተሰጠው ማረሻው የአርሶ አደሮችን ድካም በመቀነስ እርሻቸውን ለማቀላጠፍ ከማስቻሉ በተጨማሪ አርሶ አደሮች ለእርሻ የሚጠቀሙባቸውን በሬዎች በማድለብ ወደ ስጋ ገበያ በመቀየር ገቢያቸው እንዲጨምር ያግዛል።

Nov 09, 2017

ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን)

በሀገራችን ገጠራማ አካባቢዎች እስከ 5 ኪ.ግ የሚደርሱ መድሃኒቶችን ለማጓጓዝና ለማድረስ የሚያስችል ሰው አልባ አውሮፕላን ተሰርቶ የተሳካ ሙከራ ተደርጓል፡፡ በ5ሺ ሜትር ከፍታ 120 ኪ.ሜ በሰዓት የመብረር አቅም ያላት አውሮፕላኗ ደርሶ መልስ 300 ኪሜ ርቀትን ትሸፍናለች። የትራንስፖርት እጥረት ባለባቸው አስቸጋሪ ቦታዎች የህክምና ቁሳቁሶችን ለማድረስ ታስባ የተሰራች ናት፡፡

Nov 09, 2017

ክላውድ ኮምፒውቲንግ

ልዩ ልዩ መረጃዎች የሚከማቹበት ቦታ እና የኮምፒውተር ንብረቶችን መገናኘት የሚችሉበት የደንበኝነት ምዝገባ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ነው፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዳመና ማስላት ቴክኖሎጂ ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ የሳይንስ ተቋማትን በማስተሳሰር ቀደም ሲል የነበረውን ኋላ ቀር አሰራር ለማስቀረት መረጃን ከአንድ የመረጃ መረብ ክምችት በመጠቀም የነበሩትን ውጣ ውረዶችና ችግሮች ማስቀረትና የተቀላጠፈ ስራን በመስራት ከጊዜው ጋር እንዲጓዝ የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

Nov 09, 2017

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢግዚቢሽን/ትዕይንተ ማዕከል

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የራሱን እንቅስቃሴዎችና ዓለም ዓቀፍ ጥዕይንቶንን የሚሳይበት በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የበለጸገ የኢግዚቢሽን ማዕከል በመገንባት ዓለም የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ገጸበረከትን ለእንግዶች ሁሉ በማስጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡ የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ጉዟችን በማዕከሉ ውስጥ ለእይታ ወደ ቀረቡት ቴክኖሎጂዎች መሆን አለበት ብሎ እየሰራም ነው፡፡

Nov 09, 2017

የዲጂታል ቪዲዮ ኮንፈረንስ ማዕከል

የቪዲዮ ኮንፈረንስ ቴክኖሎጂ ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ ማንኛውንም ግንኙነት (ሰሚናር፤ ስብሰባ፤ አውደ ጥናት…) በአንድ ቦታ ሆኖ ለማሳለጥ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ቪዲዮ ኮንፈረንስ ማዕከል በማደራጀት እየተጠቀመ ይገኛል፡፡

Nov 09, 2017

የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ የቴሌቪዥን ብሮድካስቲንግ ማዕከል

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሃገራችን በዓይነቱና በይዘቱ የመጀመሪያ የሆነ የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ የቴሌቪዥን ብሮድካስቲንግ አገልግሎት በመጀመር በህብረተሰቡ ዘንድ የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ ባህልን ለማስረጽ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

Nov 09, 2017

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ተውህቦ እና ሃሳብ ማበልፀጊያ ማእከል

ማእከሉ ልዩ ተሰጥኦና ችሎታ ያላቸውን ዜጎች በመለየት የቴክኖሎጂ ጥማታቸውንና ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግ የሚማሩበትና የሚበለጽጉበት ሲሆን በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልልዊ መንግስት በቡራዩ ከተማ ውስጥ ግንባታው ተጀምሯል፡፡

Nov 09, 2017

ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኢስቴቲክስ እና የሃሳብ መስፋፋት ማዕከል

ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ማዕከሉ ልዩ ችሎታና ክህሎት የተሰጣቸው ዜጎችን ለይቶ ለይቶ ለቴክኖሎጂ ያላቸውን ፍላጎት የሚያረካ የማስተማር እና መንከባከቢያ ማዕከል ነው ፤ ግንባታውም ቀደም ሲል በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡራዩ ከተማ ውስጥ ተጀምሯል _፡፡

Nov 09, 2017

የሳይንስ ካፌዎች

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሀገራዊ ሳይንሳዊ እና ቴክኖሎጂካዊ አስተሳሰብንና ባህልን ለመገንባት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች የሳይንስ ካፌ በማቋቋም ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የሳይንስ ካፌዎችን ገንብቷል፡፡ እየገነባምይገኛል፡፡

Nov 09, 2017

ኤች ፒ ሲ

በኢንጂነሪንግ፣ በሳይንስ፣ በቢዝነስና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ መረጃን ለመተንተን የሚያስችል አቅም በመፍጠር ያሉብንን ችግሮችን ለመፍታት ሃይ ፕሮርማንስ ኮምፒውቲን /High Performance Computing/የ200 ቴራ ፍሎፒ /200 TF HPC/ አቅም መገንባት ወሳኝ በመሆኑ ትልልቅ መረጃዎችን መተንተን የሚስችል አቅም እየገነባ ይገኛል፡፡ ይህ የቴክሎጂ አቅም የሀገር ውስጥ ተመራማሪዎች ትላልቅ መረጃዎችን በሀገር ውስጥ እንዲተነትኑ በማስቻል ወደ ውጭ ልከው በሚያስተነትኑበት ጊዜ የሚወጣውን የጊዜ እና ገንዘብ ብክነትን ይቀንሳል፡፡

Nov 09, 2017

ኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዢ ሥርዓት(e-GP)

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዢ ሥርዓት (e-GP) እና የአፈፃፀም ስትራቴጂ በፋይናንስ ሚኒስቴር በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ይፋ ሆኗል፡፡ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የበለጸገው አሰራር የግዢና የፋይናንስ ስርዓቱን እንደሚያዘምነው ታምኖበታል፡፡

Nov 09, 2017