በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አሀመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከፍተኛ የአየር ንብረት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል።
በውይይቱ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ በረሃማ ቦታዎችን ያለማችበትን መንገድና የቴክኖሎጂ የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቆላማና በረሃማ የሆኑ አካባቢዎች ለማልማት የሙከራ ስራዎችን ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን፣ ባለሙያዎችን እና መሳሪያዎችን ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ሂደት ይጀመራል ብለዋል።
በሚኒስትር ዴኤታው የተመራው ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ከብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ፣ ከተፋሰስ ባለስልጣን፣ ከሰው ሰራሽ አስተውሎ ማዕከል፣ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት፣ ከኢንፎርሜን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችን የያዘ ነው።