በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ለሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እየተሰጠ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክቡር በለጠ ሞላ (ፒኤች ዲ) የስልጠና መድረኩን በንግግር ከፍተውታል።

እንደ ዶክተር በለጠ የስልጠናው ዓለማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘርፉን ጉዳይ ለሚከታተሉ ቋሚ ኮሚቴዎች የተሟላ ግንዛቤ ይዘው ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ በቀጣይ ለሚያከናውኑት ስራ ክትትልና እገዛ እንዲያደርጉልን ለማስቻልና የመ/ቤቱንና ተጠሪ ተቋማትን ስራዎችና ዕቅድ የምናስተዋውቅበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር በለጠ አክለውም በመ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ስላለው የሰው ኃብት ልማት፣ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ማስፋፋት ስራዎች ውጤታማነት የምንሄድበትን አቅጣጫ በመገንዘብ ክትትልና እገዛ እንዲደረግልን እንዲያግዝ ያለመ ስልጠና ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ኬይረዲን ተዘራ (ፒኤች ዲ) ባደረጉት ንግግር ይህ ሚ/ር መ/ቤት ለሃገሪቱ ያለውን ወሳኝና የማይተካ ድርሻ እንዳለው እንረዳለን፣ በተለይም መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሚከታተለው ነው።

ይህ ስልጠና የበለጠ ክትትልና አገዛ ለማድረግ ስለ ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን፣ሰፔስና መሰል የሳይንስ ዘርፎችን ግንዛቤ እንዲኖረን መደረጉ ተቋሙን በጠራ እውቀት ለመደገፍ ስለሚያስችል ለተሰጠው ትኩረት እናመሰግናለን ብለዋል።

በስልጠና መድረኩ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ፣ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ፣ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ፣ባዮ ቴክኖሎጂ፣አዕምሯዊ ንብረት እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ በሚሉ ርዕሶች ላይ ከሚ/ር ቤቱና ተጠሪ ተቋማት በመጡ ከፍተኛ አመራሮች ገለፃ ተሠጥቶባቸው ውይይት ይደረግባቸዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook