በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት ትብብርና ቅንጅት ወሳኝ ነው:- ዶ/ር አህመዲን መሐመድ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተጠሪ ተቋሙ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ስር የነበረውን ህንፃ ለመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መስሪያ ቤት ይሆነው ዘንድ የማረካከብ ስራ አስጀምሯል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ)፣ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል አህመድ ሃምዛ፣ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን ቀሬ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሳንዶካን ደበበ ርክክቡን በማስጀመር በዘርፉ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) እንደ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ያሉ ተቋማት ለቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ስላላቸው በዘርፉ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት በጋራና በትብብት መስራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገሪቱን የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ከግብ ለማድረስና ሀገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በዘርፉ የሚሰሩ ተቋማትን ችግር መቅረፍ እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የአዲሱ ህንፃ ርክክብም የዚህ አንዱ አካል ነው ብለዋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለዋና መስሪያቤት የሚሆን የቢሮ ህንፃ ስላልነበረው ስራዎችን በሙሉ አቅም ለመስራት ሲቸገር ቆይቷል።አዲሱ ህንፃ የተሟላ መሰረተ ልማት የተዘረጋለት በመሆኑ ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት ትክቅ አስተዎፅኦ ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook