ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር የተመሰረተው የትብብር መድረኩ የግል ድርጅቶቹ በሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት አካል እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡
ድርጅቶቹ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ፣ ኤሌክትሮኒክ ንግድ፣ በፋይናንሽያል ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በትምህርት ቴክኖሎጂና በመደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ፒ ኤች ዲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኃላፊነት የዘርፉን ማነቆዎች መፍታትና አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር እንጂ ዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ የቴክኖሎጂ ዘርፉን መምራት ያለበት የግሉ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንደ መንግስት የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ሕጎችን እያሻሻልን ነው ያሉት ሚኒስትሩ የግሉ ዘርፉ ደጋፊ ከመሆን ወጥቶ ሃብትና የስራ እድል ፈጣሪ እንዲሆን አሳስበዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና የአሊባባ የሥራ ፈጠራ ፕሮግራም በጋራ ባዘጋጁት ሥልጠና ልምድ ማግኘታቸውንና ይህንን ልምድ በመጠቀም መድረኩን ወደ ከፍተኛ አቅም እንደሚቀይሩት ተናግረዋል፡፡