በአይሲቲና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ክዋኔዎችና ቀጣይ ተግባራት ላይ የተመለከተ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች፣ ፈጻሚዎችና ባለድርሻ አካላት የተገኙበት ጉባኤ በኢንተር አዲስ ሌክዠሪ ሆቴል ተካሂዷል።

በመድረኩ የዘርፉ ታሪካዊ ዳራና ዐበይት ክንውኖች፣ የአይሲቲ ዘርፍ የ2014 በጀት ዓመት ቁልፍ ተግባራት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዐመታዊ እቅዶችና ዋና ዋና ፕሮጀክቶች፣ ነባር ኩነቶችና አዲሱ አዋጅ እንዲሁም የህግ ማዕቀፍች ቀርበው ተመክሮባቸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ አሊ መሰል የምክክር መድረኮች መደረጋቸው ዘርፉን ለማሳደግ ከነባሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል፣ የተሻሉ አሰራሮችን በመፍጠር ወደ ምንፈልገው ግብ መድረስ ያስችለናል ብለዋል፡፡

ክብርት ሁሪያ አክለውም ሁሉም ፈጻሚና አስኀጻሚ የዘርፉን አዋጆቹንና የህግ ማዕቀፎችን በትኩረት ተመልክተው መረዳት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ ልማት ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል አብዮት ሲናሞ (ፒ ኤችዲ) በመድረኩ በሰጡት ማብራሪያ የአይሲቲና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ነው።

ዘርፉ በእድገታችን ላይ ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ የሚጠበቅብንን ስራ ያለ እረፍት በማከናወን ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ከተሳታፊዎችም የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታውን በማሳለጥና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተገልፀዋል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook