የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ብሄራዊ ኮሚቴ ሁለተኛውን የብሄራዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አካሂዷል። ብሄራዊ ኮሚቴው የፕሮጀክቱን የ 6 ወር አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ 6 ወር ሊሰሩ በተቃዱ ስራዎች ዙሪያ ተወያይቷል።
የብሄራዊ ኮሚቴው ስብሳቢ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ በኢትየጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ስር የሚሰሩ ስራዎች የኢትዮጰያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጠኑ በመሆናቸው በፍጥነትና በጥራት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።ባለፉት ስድስት ወራት ከፕሮጀክቱ የባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ የግዢ ስራዎች መሰራታቸው የተነሳ ሲሆን በቀጣይ ወራት ደግሞ መሬት የወረዱ እና ባለፈው 6 ወር ያልተሰሩ በረካታ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ኘሮጀክት እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በፕሮጀክቱ የተካተቱ ዋና ዋና ተቋማት ናቸው።