በኢትዮጵያ ልዩ የሆኑ 3ሺ ፎቶዎችን በዲጂታል መልክ ለቱሪስቶች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

በኢትዮጵያ ልዩ የሆኑ 3ሺ ፎቶዎችን በዲጂታል መልክ ለቱሪስቶች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ለሽያጭ ማቅረብ የሚችሉበት አሰራርም አብሮ እየተዘረጋ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፉን ማዘመን የሚያስችላቸውን ስምምነት አድርገው ወደ ስራ ገብተዋል።

የስምምነቱ አንዱ አካል የሆነው የተመረጡና ባለቤታቸው ባህልና ቱሪም ሚኒስቴር የሆነ 30ሺ ፎቶዎችን በኦንላይን ለእይታ ማቅረብ የሚያስችል አስራር እየተዘረጋ ነው።

ፎቶ መግዛት የሚፈልጉ ቱሪስቶች የሚፈልጓቸውን ፎቶዎች ባለቡት ቦታ ሆነው እንዲገዙና በፈለጉት መጠን ተሰርቶ እንዲላክላቸው የሚያስችል አሰራር ነው።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማኔጀር አቤል ሰለሞን የሀገራችን የፎቶ ግራፍ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን በዚህ ስርዓት ውስጥ በማስገባት ለሽያጭ የሚያቀርቡበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድም ይመቻቻል ብለዋል።

በኢኮሜርስ አማካኝነት ፎቶዎች ለሽያጭ ቀርበው የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚያስችል አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።

ወደ ስርዓቱ የሚገቡት ፎቶዎች መውረድ የማይችሉ፣ ባለቤት ያላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ ሲሆኑ ስርዓቱ ለስራ ፈጠራ፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

ቱሪዝምን ዲጂታል ማድረግ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ አንዱ አካል ነው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook