የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ብሄራዊ ኮሚቴ የፕሮጀክቱን የ2014 ዓ.ም በጀትና የስራ እቅድ አፀድቋል።
ብሄራዊ ኮሚቴው በፕሮጀክቱ ስር በዚህ አመት ሊሰሩ በታቀዱ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
በፕሮጀክቱ ስር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱ ሲሆን የስራ ዝርዝራቸውና በጀታቸው ቀርቦ ፀድቋል።
በዓመቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን ወደ መሬት የማውረድ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።
የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን ማስፋፋት፣ የህዝብ ተቋማት ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ዝርጋታ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ስራ፣ የግል የቴክኖሎጂ ተቋማትን አቅም መገንባት በስራው ውስጥ የተካተቱ ናቸው።