በዚህ አመት 400 የመንግስት አገልግሎቶች በኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተመረጡ የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና ለሁሉም ክፍለ ከተማ ባለሙያዎች ሰጥቷል።

ስልጠናው ባለሙያዎቹ በኦንላይን የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሳይቆራረጡ ለዜጎች እንዲደርሱ ለማድረግ የሚያስችላቸው ነው።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በለሙ መተግበሪያዎች ላይ የሚሰጡ 168 አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ ይገኛሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የኦንላይን አገልግሎት ዜጎች በወረዳና ቀበሌ ጭምር ቅሬታ የሚያነሱባቸውን የመንግስት አገልግሎቶች በተቀላጠፈና ተጠያቂነት በተሞላበት መልኩ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

የዜጎችን እንግልት ለመቀነስና ጊዜና ጉልበትን ለመቆጠብ የመንግስት አገልግሎቶችን ኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ በሚቀጥሉት 10 አመታት 2,500 የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ሰልጣኞቹ በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጡ የኦንላይን አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ እንዲሰጡ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በ2014 ዓም 400 የመንግስት አግልግሎቶችን ኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ ነው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook