ስምምነቱን የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ከሳሀራ በታች የአፍሪካ ክፍል ፕሬዘደንት ሚስተር ራጋቭ ፕራሳድ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲኤታ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) ፈርመውታል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ማስተርካርድ አካታች ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ አነስተኛ የንግድ ተቋማትን ለመደገፍ እንዲሁም የሀገሪቱን የዲጂታል ተራንስፎርሜሽን ዝግጁነትን ለማጎልበት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂዎች አማራጮችን ለመለየትና ለመተግበር በሚያስችሉ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ነው የተስማሙት።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) ስምምነቱ መንግስት ድጅታል ቴክኖሎጂዎቸን ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች በማዋልና በመተግበር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳውን ዕውን ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ያግዘዋል ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ክፍያዎችን ለመፈፀም፣ ከጥሬ ገንዘብ ዝውውር ጋር የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍና መንግስትና ዜጎችን ለማቀራረብ አይነተኛ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የቆየና የጠነከረ ግንኙነት ነበረን ያሉት በማስተርካርድ ከሳሀራ በታች የአፍሪካ ክፍል ፕሬዘደንት ሚስተር ራጋቭ ፕራሳድ፣ “ማስተር ካርድ፥ የፋይናንስ ልውውጦች አስተማማኝ፣ ቀላልና ተደራሽ በማድረግ በማንኛውም ስፍራ እና ደረጃ የሚገኙ የኅብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስተሳስር፣ የሚያበቃና አካታች የሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ ማምጣት ላይ ይሰራል።
ትብብሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ቢሊዮን ሰዎችንና ሃምሳ ሚሊዮን ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማትን በ2025 ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማምጣት የያዘነውን ግብ ለማሳካት የሚረዳን ነው ብለዋል።
ማስተርካርድ ኮርፕሬሽን፤ ማስተርካርድ በዓለም የክፍያ ኢንደስትሪ ውስጥ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን የፋይናንስ ልውውጦች አስተማማኝ፣ ቀላልና ተደራሽ በመድረግ በማንኛውም ስፍራ የሚገኙ ሁሉንም የኅብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ የሚያስተሳስር፣ የሚያበቃና አካታች የሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማምጣት የሚሠራ ተቋም ነው።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰኔ 2012 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል።