በጤናው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ ወጣቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ተባለ።

ሁለተኛው የአፍላ ወጣቶች እና የወጣቶች ጤና ሳምንት ፎረም ‹‹ ፈጠራ ለተሻለ ወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት ተደራሽነት›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የወጣቶች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግና የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ህይወት ሃይሉ በሀገራችን ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙትን ወጣቶች በጤናው ዘርፍ የላቀ ተጠቃሚ ለማድረግ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል ብለዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጀነራል አብዮት ባዩ (ፒ ኤች ዲ) ባላደጉ ሃገሮች ውስጥ የምንኖር ዜጎች የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ፣ የሕዝባችንን መሰረታዊ የጤና ችግሮች፣ የጤና መሰረተልማቶችን ማዕከል ያደረጉ የኢኖቬሽን ስራዎች ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ ወጣቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ያሉት ዳይሬክተር ጀነራሉ ዘርፉ የሁሉም ተቋማት ጉዳይ በመሆኑ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሳምንቱም በተለያዩ የወጣቶች ጉዳዮችን ባካተቱ ዝግጅቶች የሚታሰብ ሲሆን የመጪው ትውልድ ጤናን ለማሻሻል የዲጂታል ጤና ስርዓትን መዘረጋት ላይ ትኩረት አድርጎ ይከበራል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook