በፌዴራል እና በክልሎች መካከል ያለው የቴክኖሎጂ ደረጃ በጣም የተራራቀ በመሆኑ በቀጣይ በክልሎች የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን የማጎልበት ሥራ እንደሚሰራ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

ይህ የተባለው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከክልሎችና ከከተማ መስተዳደር የሥራ ሓላፊዎች ጋር ለቀጣይ 10 ዓመት ባዘጋጀው ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና ዕቅድ ላይ በመከረበት ወቅት ነው።

በኢትዮጵያ ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬት እና የሰው ሀብት ቢኖርም ሀገሪቱ የምትጠቀመው ቴክኖሎጂ ዝቅተኛ በመሆኑ ኢኮኖሚዋ ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጓል ተብሏል።

ለዚህም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅ አቅም ውስንነት በመሠረታዊ ምክንያትነት ተጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈ ቴክኖሎጂዎችን ለመገንባት የሚያስችሉ የመሠረተ ልማት ችግሮች መኖር ሌላው ምክንያት ነው ተብሏል።

በመሆኑም በቀጣይ 10 ዓመታት እነዚህን ችግሮች በመፍታት የቴክኖሎጂው ዘርፍ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረከት ታልሟል። በምክክር መድረኩ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በፌዴራል እና በክልሎች መካከል ያለው የቴክኖሎጂ ደረጃ በጣም የተራራቀ በመሆኑ በቀጣይ በክልሎች የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን የማጎልበት ሥራ ይሠራል ብለዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook