ቪንት ሰርፍ ለዓለም አቀፉ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ኢትዮጵያን ያደረገችውን ዝግጅት አደነቁ።

ቪንት ሰርፍ ለዓለም አቀፉ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ኢትዮጵያን ያደረገችውን ዝግጅት አደነቁ።

=========================================

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) የኢንተርኔት አባት በመባል ከሚታወቁት ቪንት ሰርፍ ጋር ተወያይተዋል።

ቪንት ሰርፍ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የበይነ-መረብ አስተዳዳር ጉባኤ ያስተናገደችበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑንና በዚህም መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማዘጋቷ በበይነመረብ አስተዳዳር ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየችበት ነው ብለዋል።

ቪንት በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያውያንን እንግዳ ተቀባይነት ማየታቸውንም ተናግረዋል።

የአኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ቪንት ሰርፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጉባኤው በመሳተፋቸው እና ለዓለም አቀፉ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ልምዳቸውን በማካፈላቸው አመስግነዋቸዋል።

በቀጣይም አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook