ቴክኖሎጂን በማልማት በማሸጋገርና ሀብት ለመፍጠር እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባህል የዳበረበት ሕብረተሰብ ለመገንባት የሁሉም አካል የተቀናጀ ርብርብ ይጠበቃል።

ከ ሰኔ 21 – 22/2014 ሲካሄድ የነበረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ተጠሪ ተቋማትና የክልል የዘርፉ ቢሮዎች የበጀት ዓመቱ የእቅድ አፈጻጸምና የ2015 ተግባራት አቅጣጫ ላይ ያተኮረው ውይይት ተጠናቋል።

የመድረኩ የመጀመሪያ ቀን በዓመታዊ እቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ሲሆን የሁለተኛው ቀን ቆይታ የዘርፉን ፖሊሲ፣ ስትራቴጅዎችና ዕቅዶች ወደ ክልል ቢሮዎች፣ በተዋረድ በሚገኙ አስፈጻሚዎችና ፈጻሚዎች ማድረስና ፈጻሚዎችን እንዴት ማብቃት እንደሚገባ አተኩሮ መክሯል።

በውይይቱ ማጠናቀቂያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ክቡር ባይሳ በዳዳ(ፒኤችዲ) በ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ከክልሎች የቀረበው ሪፓርትና የተደረገው ውይይት ለ2015 በጀት ዓመት አቅም የሚፈጥር ግብዓት የተገኘበት ነው ብለውታል።

እንደ ዶክተር ባይሳ የዘርፉን ተግባራት በእውቀት ለመምራት እና ሪፖርቱን በተጨባጭ ውጤቶች ለማሳየት የተደረገው ጥረትም የሚበረታታ ነው ብለውታል።

ነገር ግን ይላሉ ዶክተር ባይሳ ሪፖርቶቹ ከአገር በቀል የኢኮኖሚ እድገት አቅጣጫና ከምናገለግለው ሕዝብ ፍላጎት አኳያ ምን ችግር ለይተን፣ ምን አቅደን፣ ምን አሳካን? ከተሰጡን ተልዕኮዎችና አገራዊ ኃላፊነቶች አኳያ የዘርፉን አስቻይነት ሚና በመገንዘብ ቅድሚያ የተሰጣቸውን የኢኮኖሚ ሴክተሮች ከመደገፍ፣ ከማብቃትና የተለዩ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ምን አሳካን የሚሉት ሊዳሰሱ ይገባ ነበር ብለዋል። እነዚህ ነጥቦች ወደ ክልሎችና ቢሮዎች ስንመለስ ከቀጣይ እቅዶች ጋር ተዳስሰው መመለስ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒኤቺዲ) ዘርፉን ለመምራት ኢትዮጵያ የሰጠችንን ተልዕኮ ስንቀበል በየደረጃው እምቅ የመምራትና የመስራት አቅም እንዳለ በመተማመን ነበር። በዚህ በጀት ዓመት አገራችን በበርካታ ችግሮች ውስጥ ሆናም አበረታች ውጤት መመዝገቡን ከሁሉም ክልሎች ከቀረቡት ሪፓርቶች ተገንዝበናል። ይህም የነበረንን ግንዛቤ እንድናረጋግጥ አድርናል ብለዋል።

በዚህ ፈታኝ ወቅት እና በተበታተነ የትኩረት ማዕከል ውስጥ ሆኖ ከተልዕኮ ሳይዛነፉ ስራን መምራት ለቻሉ ቢሮ ኀላፊዎች ምስጋና አቅርበዋል።በየክልሎች የተመዘገቡት ለውጦች በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዓመታዊ እቅድም ሆነ በቀጣይ የዘርፉ የአስር ዓመት ዕቅድ ላይ የተጠሪ ተቋማት፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች ልምድ ቀስመው፣ የተሟላ ግልጽነትና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለ2015 በጀት ዓመት እቅድ ተግባራዊነት የሚዘጋጁበት አቅም የፈጠረ ነው ብለውታል።

የዘርፉ አመራሮች ከአስር ዓመቱ የዘርፉ እቅድ የተቀዳ የየራሳቸውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ተጨባጭ እቅድ ሊያወጡ ይገባል ያሉት ዶክተር በለጠ፤ በቀጣይ በአገራዊ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፓሊሲ፣ በኢትዮጵያ 2025 የድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ የተሟላ ግንዛቤ መያዘና የጋራ መግባባት መፍጠር ይጠበቅብናል ብለዋል።

ዶክተር በለጠ ሞላ አክለውም የኢኖቬሽንና እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በዘርፉ የተሰማሩ አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በረዥም፣ መካከለኛ እና ዓመታዊ እቅዶች ማለትም የ10 አመት የዘርፍ የልማት እቅድ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂና በ2015 ዓ/ም መነሻ እቅድ ላይ የተቀመጡት አጠቃላይ አቅጣጫዎችን ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባህል የዳበረበት ሕብረተሰብ ለመገንባት መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በሁለቱ ቀናት ከቀረቡት ሪፖርቶችና መነሻ እቅዶች በተደረጉ ውይዬቶች በቀሪ ወራት በቅድሚያ መታየትና እንደ አመራር ዘርፉ የሚፈልጋቸውን ድጋፎች በመለየት ማገዝ የሚያስችል መረጃ ተገኝቷል።

ክቡር ሚኒስቴሩ አክለውም ከውይይቱ የተገኘፈኙትን ተሞክሮዎች ቀምረን ለማስፋት፣ የተገኙ ግብአቶችንና ጥቆማዎችን ደግሞ የ2015 እቅዶቻችንን ለማዳበር እንጠቀምባቸዋለን ብለዋል።

ዘርፉ ለአጠቃላይ የአገራዊ እቅዶች መሳካት ቀጥተኛና ጥብቅ ቁርኝት ያለው መሆኑን መገንዘብ መቻላቸውን አውስተው መላው የሚኒስቴር መቤቱና በልዩልዩ ደረጃ ያሉ አመራሮችና ሙያተኞቻችን ትኩረት ሊሰጧቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች እንደአሉ ክቡር ሚኒስቴሩ በአጽንኦት አሳስበዋል።

እንደ ክቡር ዶክተር በለጠ በሚንስቴር መ/ቤት ደረጃ የመስሪያ ቤቱ አንኳር ተልእኮ የአስተባባሪነት፣ ፖሊሲ አውጭነት፣ የማስፈፀም አቅም ግንባታና ቁጥጥርን ጭምር መምራት ነው። ሚኒስቴር መስሪያቤቱ፣ ተጠሪ ተቋማቱና በክልል የሚገኙ ቢሮዎቻችን ከመንግስት ተለይተው የተሰጧቸውና የሚያከናውናቸው ተልዕኮዎች በተፈጥሮ ፈጣን ተለዋዋጭ ሁኔታ ምርትና አገልግሎቶችን ለአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና የፓለቲካ አስተዳደራዊ መስኮች ውጤታማነት፣ ከፍተኛ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ጋር በቀጥታ የተቆራኙ ናቸው።

ስለሆነም ተልዕኳችን የማይዳስሰው፣ የማይመለከተው የኢኮኖሚና የአገልግሎት ዘርፍ የለም። የዚያኑ ያክል በሌሎች ዘርፎች ያለው የግንዛቤ ደረጃም ይለያያል። በተወሰኑ ዘርፎች ባሉ የተዋረድ ቢሮዎች የተሻለ ግንዛቤ ሲኖር በሚበዙት ያለው ግንዛቤ ውስን ወይም እዚህ ግባ የማይባል ነው።

ስለዚህ ዘርፉን በተመለከተ ያለውን ውስን የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግ፣ ቴክኖሎጂን የመቀበል፣ የመጠቀም፣ የማሻሻልና የመፍጠር ክህሎት ደረጃ እስኪመጣ ያልተቋረጠ የስርፀት ይጠበቅብናል ብለዋል።በመሆኑም የሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የክልል የሴክተሩ መሪ ተዋናይ አካላት የሰው ኃይልና አመራር ይህንን መሪ እቅድ በማዳበርና በመፈፀም በሂደትም እንደአስፈላጊነቱ የመከለስ ተግባርን በላቀ ተሳትፎና ባለቤትነት ሊሳተፉበት ይገባል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዘርፉ ከሌሎች ዘርፎች ጋር ያለውን ሰፊ ተዛምዶና አንዳንድ ጊዜም አስገዳጅነት ባህሪ በሚመለከት ያሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት ሌሎች ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቶች ካላቸው የተለመደ የአሰራር፣ የተልእኮና የትግበራ አውድ እንዲወጡና ተቀራርበን ለመስራት የሰፋ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል።

በአስር ዓመቱ የእቅድ ወሰን ለዘርፋችን የተቀመጡ ሰፋፊ አገራዊ እቅዶች መነሻነት አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ተጨባጭ የእድገት ደረጃ እና ወደፊት ልታሳካው የምታስበውን ርእይ ግምት ውስጥ ያስገቡ ዘርፍ ተኮር እቅዶችን በየክልላችን ማቀድ አለብን።

ለእቅዶች ተፈጻሚነት ተጨባጭ ግቦችን፣ መለኪያና ማሳያዎችን አስቀምጠን ቀየደረጃው ያሉ ተዋንያንን ለማሳተፍና ለ ማብቃት ሰፊ ርብርብ እንዲደረግበት አሳስበዋል።ተሳታፊዎች በበኩላቸው የአደረጃጀት ችግሮች እንዲፈቱላቸው፣ የአሰራርና የበጀት ማነቆዎች እንዲቃለሉ፣ ዘርፉ በየክልል አመራሮች ተገቢ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ የሚያስችል ድጋፍ ከፌደራል መንግስት እና ከሚኒስቴሩ ይጠበቃል ብለዋል።

በሁለቱ ቀናት ውይይት የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች ከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆንየ2014 ዓም እቅድ ክንውን፤ የዘርፉ የአስር ዓመት መነሻ እቅድ፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና ቀጣይ አቅጣጫዎች ቀርበው ተመክሮባቸዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook