‹‹የባሉበት ትምህርት (online Education) ዘርፉን በመልካም ጎን ይቀይረው ይሆን?›› በሚል የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የበይን መረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ትምህርትን በቴክኖሎጂ መደገፍና በሚቻልበት ሁኔታ፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) ትምህርትን በመማሪያ ክፍል በመወሰን ሁሉም ተማሪዎች በአንድ እንዲቀበሉት የሚያደርገውን አሰራር በመቀየር ተማሪዎች በያሉበት ሆነው በራሳቸው ትምህርን የመቀበል ፍጥነት እንዲማሩ ማድረግ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ቴክኖሎጂን በትምህርት ስርዓት ውስጥ በማካተት ተማሪዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅ፣ ዜጎች የዲጂታል እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ባለሙያዎችን ማሰልጠን፣ አስተማምኝ የበይነ መረብ ግንኙነት መሰረተ ልማት መገንባት ላይ እየተሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ጥራና አግባብነት ኤጄንሲ ጀነራል ዳይሬክተር አንዷለም አድማሴ (ፒ እፕች ዲ) የባሉበት ትምህርትን በተደራጀ መልኩ ለመስጠት መመሪያ ተዘጋጅቶብወደ ስራ ተገብታል ብለዋል።
ለ4 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ በመስጠትም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሉበት ትምህርትን (online Education) መስጠት ጀምራለች ብለዋል።
ትምህርት ጥራት ላይም አሉታዊ ተፅኖ እንዳታሳድር ጠንካራ ስራ እየተሰራ ስለምሆኑ ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ 2025 ውስጥ የዲጂታል እውቀት መገንባት አንዱ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ ተቀምጧል፡፡