ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጡ።

ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጋር መክረዋል።

በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሰለሞን ነጋሽ፣ በአትላንታ የኢንፎርሜሽን ሲስተም አርክቴክቸር ባለሙያ የሆኑ አህመድ ጀማል እና በ ቨርጂኒያ የመረጃ እና የመሰረተ ልማት ደህነነት አማካሪ የሆኑት ፍስሃ ደስታ ሀገራቸውን በዘርፉ ለማገልገል እንደሚፈጉ ተናግረዋል።

የዲጂታል አግልግሎቶች ጥራት እና ደረጃን በማስጠበቅ፣ በዲጂታል ሴኩሪቲ፣ በዲጂታል ኦዲትና በዲጂታል ኢኖቬሽን ላይ ያላችውን እውቀት ለማካፍል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዘርፉ የተስማሩና በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን በማስተባበር ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዲያስፖራዎቹ ሀገራቸውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በመምጣታቸው አመስግነው ስል ኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ገለፃ አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በዘርፉ የባለሙያዎችን አቅም ለመጠቀምና በትብብር ለመስራት ተቋሙ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል።

ባለሙያዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው የዲጂታል ፎረም ላይ እንደሚሳትፉ እና ተሞክሯቸውን እንደሚያጋሩ አስታውቀዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook