አዲስ የተመደቡ ዲፕሎማቶች ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ተግባራዊነት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ

ለዲፕሎማቶቹ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዲፕሎማቶች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ዕቅድን በሚገባ ተረድተው፣ በተመደቡባቸው ሀገራት ለሚገኙ ለትውልድ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ወገኖች በሚገባ በማስተዋወቅና ለስትራቴጂውም ተግባራዊነት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ማስተባበር እንደሚጠበቅባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለፀዋል፡፡

ዲፕሎማቶቹ የዐሥር ዓመቱን የልማት መሪ ዕቅድና ሌሎች ሀገራዊና የዘርፍ ዕቅዶች በማወቅ ለዕቅዶቹን ትግበራዊነትም ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ስትራቴጂው ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማኑፋክቸሪንግና በቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶች መለየታቸውን፤ ስትራቴጂውን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችሉ ሶስት አቅጣጫዎችን መከተሉን የገለጹት ደግሞ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር አህመዲን መሐመድ ናቸው፡፡

ዲፕሎማቶች እንደ ሀገሩ ተጨባጭ ሁኔታ ከውጤት በመነሳት የውጤቱ ምክንያት የሆነ ቴክኖሎጂን መለየትና ወደ ሀገር እንዲመጣ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook