አገልግሎቶች

ዳታ ማዕከል ግንባታ

ተቋሙ ዳታ  ማዕከላትን መገነባት የሚፈልጉ ኩባንያዎችን የራሳቸውን የግል ሥፍራዎችን ላይ መገንባት ሳያስፈልጋቸው ዳታ ማዕከላት እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡
ሚኒስቴሩ የግል የዳታ ማዕከል ኪራይ፣ ሰርቨር በመከራየት በጋራ የዳታ ማዕሉን አገልግሎት መጠቀም  ወይም ደግሞ ከእነዚህ ሁለት አማራጮች በማቀናጀት የሚጠቀም ይሆናል፡፡ የዳታ ማዕከል እንደ አገልግሎት (DCAAS)  አገልግሎቱን የሚያገኙት ተቋማት ከሚገኙበት ስፍራ ውጪ የሆነ የዳታ ማዕከል አገልግሎትና መሰረተ ልማት ለተገልጋዮች ማቅረብ ነው፡፡ ደንበኞች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የዳታ ማዕከል በኪራይ ወይም በሊዝ  በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለቤትነት ስር የሚገኙ ሰርቨሮችን፣ ኔትዎርክ አገልግሎቶችን፣ መረጃ ማከማቻን እንዲሁምየኮምፕዩተር ግብዓቶችን ይጠቀማሉ፡፡

የኢሜል አገልግሎቶች

ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የኢሜል አድራሻዎችን ለማግኘት በመንግስት ይፋዊ የደብዳቤ ጥያቄ መሰረት የሚቀርቡ አገልግሎቶቸ ናቸው  ፡፡ እነዚህ የኢሜይል ሰርቨሮች እያደገ የሚሄድ ፍላጎት መሸከም የሚችሉ፣ ለአጠቃቀም ቀላል  እና የላቀ ድጋፍ ያላቸው  ናቸው፡፡ ሚኒስቴሩ ለመንግስት ተቋማቱ በጥያቄያቸው መሰረት የሚያቀርበው የኢ-ሜይል አካውንት (አድራሻ) ሜየላቸውን በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ስፍራ እንዲሁም በማንኛውም መገልገያ መሳርያ ላይ ላይ ያለምንም መቆራረጥ መጠቀም ያስችላቸዋል፡፡

የአጭር መልዕክት አገልግሎቶች

·         ሚንስቴሩ በአስቸጋሪ ወቅቶች ጊዜ ደንበኞች ወሳኝ ግንኙነቶችን የአጭር የፅሁፍ መልዕክት በመጠቀም እንዲያቀርቡ ያግዛቸዋል፡፡

·         አለም አቀፋዊ የስልክ ቁጥሮችን እና ብልህ ራውቲንግ በመጠቀም፣ በተደጋጋሚ ለተጠቃሚዎች ማሳሰብያዎችን ይልካል እንዲሁም ተጠቃሚዎችን በሰፊው መድረስ ይችላል፡፡

·         መነሻ ያላቸው ማስጠንቀቂያዎችን ይፈጥራል እንዲሁም ምላሾችን የአጭር ፅሁፍ መልዕክት ኤፒአይ በመጠቀም በፍጥነት ይመልሳል