ኢትየጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ዝርዝር ተግባራት ላይ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በባዮ ቴክኖሎጂ፣ በህዋ ሳይንስ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው፡፡

እስከ 2025 በሚቆየው ይህ የትብብር ስምምነት የሰው ሃይል ስልጠና፣ የባለሙያ ልውውጥ፣ በኢኖቬሽን ሰታርትአፕ እና በሌሎች የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡

መሰከረም ወር ላይ የተቋቋመው የሁለቱ ሀገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ያዘጋጀውን የትብብሩን ዝርዝር ተግባራት ሰምምነት በኢትየጵያ በኩል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) እና በደቡብ አፍሪካ በኩል ድግሞ የሳይንስና ኢኖቬሽን ዲፓርትመንት ተወካይ ሚስተር ዳን ዱ ቶይት ፈርመወታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ፣ በምርምር እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ደቡብ አፍሪካ ያላትን የተሻለ ልምድ ኢትዮጵያ ትወስዳለች ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ከዚህ በፊት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook