ኢትዮጵያ ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር እየፈጠረች በመሆኑ አለም አቀፍ ተቋሟት በዘርፉ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ጥሪ አቀረቡ።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው 19ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ ተጠናቋል።

የዲጂታል ይዘትና አገልግሎት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ 26 በላይ ድርጅቶችና ከ390 በላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ታሳታፊዎች ታድመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር እየፈጠረች በመሆኑ አለም አቀፍ ተቋሟት በዘርፉ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በቴሌኮም ዘርፍ የተጀመረው ማሻሻያ ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ያሉት ሚኒስትሩ አጋር አካላት፣ አለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያግዙ የዲጂታል ይዘትና አገልግሎቶች ላይ እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ይዘቶችና እና አገልግሎት ላይ ለሚሳተፉ አካላት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል። በ19ኛው የዲጂታል አፍሪካ ጉባኤ ላይ ከ 26 በላይ ሀገራት የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ካምፓኒዎች እና የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎች ተሳትፈዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook