ኢትዮጵያ በቀጣይ አመት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የአለም አቀፍ የቴሌኮሙኔኬሽን ልማት ጉባኤ ዝግጅት አህጉራዊ ስብሰባዎችን እንድትመራ ተመረጠች።

የ2021ንዱ አለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በቀጣይ አመት አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።

ለጉባኤው ስኬት ኢትዮጵያ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገች ሲሆን የጉባኤውን አህጉራዊ ስብሰባዎች በሊቀመንበርነት እንድትመራም ተመርጣለች።

ስብሰባውን በሊቀመምበርነት እንዲመሩ የተመረጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው አህመዲን መሀመድ (ፒ ኤች ዲ) ለጉባኤው መሳካት ውጤታማ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንደሚያከናወኑ ቃል ገብተዋል።

በአህጉራት መከካል የሃሳብ ልውውጥ በማድረግ፣ ፍሬያማና ቀልጣፋ የዝግጅት ስራዎች እንዲከናወኑ ኢትዮጵያ ትሰራለች ያሉት ሊቀመንበሩ በኮቪድ ተፅዕኖ ውስጥ ስኬታማ ስራ እንደምታከናውን ቃል ገብተቃል።

የጉባኤው አስተናጋጅ ሀገር አህጉራዊ ስብሰባዎችን እንድትመራ መደረጓ ለኮንፈረንሱ የሚደረጉ ዝግጅቶች በፍጥነት እንዲከናወኑ እድል ይሰጣል።

ኢትዮጵያ 2021ንዱን የአለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ጉባኤ የምታስተናግድ ሲሆን ከተሳታፊ ሀገራት የቀረቡ ኮቪድ የደቀናቸው ስጋቶችን የተመለከቱ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አቅርባለች።

ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተወጣጡ 325 ሃላፊዎችና ተወካዮች የተሳተፉበት ስብሰባ በበይነ መረብ ተካሂዷል።

በኮቪድ 19 ምክንያት ጉባኤው በአካል ይካሄድ ወይንም በበይነ መረብ የሚሉት አማራጮች ላይ ሀገራት የተለያዩ ሃሳቦችን እያነፀባረቁ ነው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook