ኢትዮጵያ በ2015 የሚካሄደውን 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ታስታናግዳለች።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁርያ አሊ ከተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሉ ዤንሜን ጋር በፎረሙ ዝግጅት ዙሪያ በፖላንድ ተወያይተዋል።

በዓለም 3.7 ቢሊዮን የሚሆነው ህዝብ ምንም አይነት የቴሌኮምና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደማያገኝ የተናገሩት የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሉ ዤንሜን ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር አፍሪካውያን ይይዛሉ ብለዋል።

በአፍሪካ የበይነ መረብ ግንኙነት ዝቅተኛ መሆኑን ያነሱት ዋና ጸሐፊው ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ቀጣዩ ፎረም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚጠቆሙበት ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በበኩላቸው አፍሪካ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግና ከመሰረተ ልማት ጋር የተያያዙ ችግሮቿን ለመፍታት የምታደርገው ጥረት በዚህ መልኩ ከተደገፈ መልካም ውጤት እንደሚመዘብ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

በተለይ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ወጣት መሆኑ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ለልማት ለመጠቀም ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

ሀገራቸው ኢትዮጵያም የቴሌኮም ዘርፍ ማሻሻያ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣የዲጂታል ክህሎትና ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ሉ ዤንሚንና ቢሯቸው እያደረገ ላለው ትብብርና ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በፖላንድ እየተዳሄደ ሲሆን መድረኩ የተለያዩ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላትን በአንድ መድረክ በማምጣት ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ ፖሊሲዎች ላይ ውይይት የሚካሄድበት ነው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook