ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ውስጣዊ ችግር ለመፍታት አቅሙና ጥበቡ ያላት ሀገር ናት ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሀንስ ሄነሪስ ሉንዱኪስት ጋር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና በሌሎች ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ስዊድን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላት ሀገር በመሆኗ ኢትዮጵያ ይህንን ልምድ መውሰድ እንደምትፈልግና ድጋፍም እንደምትሻ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ስዊድን በተለያዩ መስኮች ለኢትዮጵያ በምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ በ አይ ሲ ቲ እና ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ኢትዮጵያ ያለባትን የሰው ሀይል ክፍተት ለመሙላት ስዊድን ቀደም ሲል ስታደርግ የነበረውን ትብብርና ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሚስተር ሀንስ ሄነሪስ ሉንዱኪስት በቴክኖሎጂና ስራ ፈጠራ፣ በትምህርትና ግብርና ዘርፍ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ ከ 13 በላይ የስዊድን ካንፓኒዎች እንዳሉ የገለፁት አምባሳደሩ አሁን ባለው ሃገራዊ ሁኔታ በስዊድን በኩል ያለውን ስጋት አንስተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ውስጣዊ ችግር ለመፍታት አቅሙና ጥበቡ ያላት ሀገር መሆኗን ለአምባሳደሩ አረጋግጠውላቸዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook