ኢትዮጵያ ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ የሰው ሰራሽ አስተውህሎ ዩኒቨርሲቲ ተነሳሽነት ልምድ ትወስዳለች።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የዩናይትድ አረብ ኢሚሬትን ምርምር ተኮር የሰው ሰራሽ አስተውህሎ ዩኒቨርሲቲን ጎብቷል።

ኢትዮጵያ ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ ጋር ባላት መልካም ወዳጅነት መሰረት የኢትዮጵያ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ልምድ እንደሚወስዱ ያላቸውን እምነት ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።

የአሁኑ ቴክኖሎጂ ወደ ሰው ሰራሽ አስተውህሎና ህዋ ሳይንስ ተሸጋግሯል ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያንም ወደ አዲሱ ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር ይሰራል ብለዋል።

ባለፈው አመት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ፒ ኤች ዲ) ያቋቋሙት የሰው ስራሽ አስተውሎ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በሚኒስትር ዴኤታው የተመራው ቡድን በሀገሪቱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎን ጨምሮ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ከሰው ሰራሽ አስተውሎ ማዕከል፣ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩትና ከኢንሳና የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ናቸው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook