ኢትዮጵያና ሩስያ ከዚህ ቀደም የነበሩ ስምምነቶች ወደ ስራ በሚገቡበትና አዳዲስ የስምምነት ማዕቀፎችን መመስረት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ፒ ኤች ዲ)ና በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር የቭጊኒ ተርኪን ሁለቱ ሃገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ሃይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ከዚህ በምታደረገው እንቅስቃሴ ሩስያ በሰው ሃይል አቅም ግንባታ ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም ያደረጓቸው ስምምነቶች የትብብር ማዕቀፍ በመፍጠር በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ የ10 አመት መሪ እቅድ ጋር የሚጣጣሙ አዳዲስ ስምምነቶች እንዲደረጉም ጠይቀዋል።