ኢትዮጵያ የወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች ነው:- ሁሪያ አሊ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ

በፖላንድ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው 16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም እንደቀጠለ ነው።

ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፉ ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የአፍሪካ አህጉር ከ60 በመቶ በላይ ወጣቶች የሚኖሩበት እንደመሆኑ ይህንን መልካም እድል መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወጣቶች የኢንተርኔት ግንኙነትን ወደ እውቀት፣ ፈጠራ እና የስራ እድል ሊቀይሩት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በኢትዮያ ከ 15 እስከ 29 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 25 ሚሊየን በላይ ወጣቶች የሚኖሩ ሲሆን በየ አመቱ ከ3መቶ ሺ በላይ ወጣቶት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይመረቃሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ኢትዮጵያ በዘርፉ ወደ ፊት ለመራመድ እንዲያስችላት እየሰራች ያለችውን የማሻሻያ ስራዎች ለፎረሙ አብራርተዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook