ጉባኤውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን እና ኤክስቴንሽያ በትብብር የሚያዘጋጁት ነው።
በጉባኤው ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ300-500 የሚደርሱ ሚኒስትሮች፣ የቴክኖሎጂ ድርጅት ኃላፊዎች እና ከፍተኛ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) የኢኖቬሽን ዲጂታል አፍሪካ ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መደረጉ ኢትዮጵያ ተመራጭ እየሆነች መምጣቷን ማሳያ ነው ብለዋል።
ጉባኤውን ለማስተናገድ የኢትዮጵያን ዝግጁነት ያረጋገጡት ሚኒስትሩ ጉባኤው ኢትዮጵያ ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አጋዥ የሆኑ የመፍትሄ ሃሳቦችን የምታገኝበት እንደሚሆን ተናግረዋል።
ጉባኤው ግንቦት 3 እና 4/2014 ዓም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ለፖሊሲ አውጪዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የዲጂታል ቴክኖሎጂ የመፍትሄ ሃሳቦች የሚቀርቡበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።