ኢትዮጵያ 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ አዘጋጅነቷን ከፖላንድ በይፋ ተረከበች

በፖላንድ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው 16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተጠናቅቋል።

በጉባኤው ማጠናቅቂያ በ2015 የሚካሄደውን 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ከፖላንድ በይፋ ተረክባለች።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በቀጣይ አመት ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ፎረም የአፍሪካውያንን የኢንተርኔትና የመሰረተ ልማት ችግሮችን በመቅረፍ ካደጉት ሀገራት ተርታ የሚያሰልፋትን አቅም ለመፍጠር የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚጠቆሙበት እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል።

የዘንድሮው ጉባኤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን የተጋፈጥንበትና በወረርሽኙ ምክንያት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮች የተሻሉ ሆነው የተገኙበት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የዲጂታል አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ፖሊሲ አውጭዎችና ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት ግንባታ ችግር ለአፍሪካ የመጪው ጊዜ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውንም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ 17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በስኬት ለማጠናቀቅ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በቀጣይ አመት በኢትዮጵያ የሚካሄደው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም የአፍሪካ ጉዳይ ጎልቶ እንዲወጣ ይሰራል ተብሏል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook