የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዘርፉን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፎዚያ አሚን (ፒ ኤች ዲ)የዘርፉን ሀገራዊ ፋይዳ ለማጉላት ተቋማት የስራ ፈጠራ ላይ ማተኮር እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት የተገነባውና ከሳተላይት መረጃ መቀበል የሚያስችል የመሬት መረጃ መቀበያ ጣቢያ ግንባታ ተጠናቆ ከቀጣዩ ግንቦት 2013 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮያ ባዮ ቴከኖሎጂ ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀው የእንሰት ማቀነባበሪያ እና ማብላያ ቴክኖሎጂ ውጤታማ መሆኑንና ቴክኖሎጂውን ለማስፋት የሚያስችሉ ስራዋች መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
ላለፉት ዘጠኝ ወራት 65,300 የኮቪድ-19 ናሙናዋች መመርመራቸውንና በኢትዩጵያ የመጀመሪያው ከፊል አውቶሜትድ የማይክሮ አልጌ ላቦራቶሪ ግንባታ መከናወኑን የባዩ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ካሳሁን ተስፋዬ(ፒ ኤች ዲ) አብራርተዋል፡፡
በዘጠኝ ወራቱ የመንግስት መረጃዎችንና አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የ Tier- 3 ብሔራው የዳታ ማእከል ግንባታ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቅ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት ግንባታ 91% መድረሱ፣ ለዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ትግባራ በተደረገ ሀብት የማፈላለግ ስራ ከዓለም ባንክ ድጋፍ ማግኘት መቻሉ በሚኒስቴር መስርያቤት ቀርቧል፡፡
ተግባራት መሰራተቸው ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ እያሳዩ ያለው ውጤት በየተቋማቱ መታየት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በመድረኩ ላይ በቀጣይ የዘርፉን የእቅድ እና ሪፖርት ስርአት ኦንላይን ማስኬድ የሚያስችል ዳሽ ቦርድ በይፋ ወደ ስራ ገብቷል፡፡