ከፋብሪካዎች የሚመነጭ በካይ ጋዝ ለመቀነስ የሚረዱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ቀረቡ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከየአከባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከፋብሪካዎች የሚወጣውን በካይ ጋዝ ልቀት ለመቀነስና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመቋቋም አጋዥ የሆኑ በሀገር ውስጥ የተሰሩ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ዳሰሳ በማድረግ ለይቷል።

ከእነዚህም ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣ በካይ ጭስ ለማስቀረት የሚያስችል ማሽን ፣ ከሆስፒታሎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን ወደ ጭስ አልባ ከሰል መቀየር የሚችል ማሽን እና ከቆዳ ፋብሪካዎች የሚወጣ በካይ ጭስን ማስቀረት የሚያስችል ማሽን ቀርቧል።

እነዚህ የፈጠራ ስራዎች ፋብሪካዎች የሚለቁትን በካይ ጋዝ ለመቀነስ መጠቀም በሚችሉበት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

በአየር ብክለት ዙሪያ በ50 ተቋማት የዳሰሳ ጥናት የተደረገ ሲሆን ጥሩ ተሞክሮ ያላቸው ተቋማትን በመለየት የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ተደርጓል።

ከነዚህም ተሳታፊዎች በአየር ብክለት ቅነሳ ጥሩ ተመኩሮ ካላቸው ተቋማት አንዱ የሆነው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ተጎብኝቷል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook