የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከዚህ በታች በተጠቀሰው የስራ መደብ ላይ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት minthr@mint.gov.et በሚል ኢሜይል ከዚህ በታች የተጠቀሱት መረጃዎች በማያያዝ መላክ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ለተጨማሪ መረጃ 0921621417 ደውሎ መጠይቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የስራ መደቡ መጠሪያ ሾፌር መካኒክ
- የመደብ መታወቂያ ቁጥር 8.6/ኢቴ-614
- የስራ ደረጃ IX
- የመነሻ ደመወዝ 4379/ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር/
- የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ፣3ኛ ደረጃ የመንጃ ፍቃድ እና በሹፌር መካኒክነት የምስክር ወረቀት ያለው
- አግባብ ያለው የስራ ልምድ 4 ዓመት
- ብዛት 1