የመንግስት ስራዎችን በዲጂታል መልክ ለመስራት የሚያስችሉ የስራ ትስስር ማዕከላት በ6 ተቋማት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

የስራ ትስስር ማዕከላቱ የመንግስት ስራዎች በግንኙነቶች ሳይቆራረጡ፣ ጊዜና ቦታ ሳያግዳቸው በዲጂታል መልኩ እንዲሰሩ የሚያደርግ አሰራር የሚተገበርባቸው ናቸው፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለስልጣን እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጄክት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉ ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱን በጨረታ ያሸነፈው አይ ኢ ኔትወርክ ሶሉሽን የሚሰራው ሲሆን በ120 ቀናት ውስጥ አጠናቀቆ ለማስረከብ ስምምነት አድርጓል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ያለግሉ ዘርፉ ተሳትፎ እውን ስለማይሆን በሁሉም የልማት ስራዎች የግል ዘርፉ አጋር ብቻ ሳይሆን ባለቤትም እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀከት ስር በመተግበር ላይ ካሉት ስራዎች ውስጥ የመንግስት የስራ ትስስር ማዕከል ልማት አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ስርዓቱ የመንግስት ተቋማት ስራዎች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው የሚከወኑበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍ ትግበራ በ50 የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ክልሎች ጭምር ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook