ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ባካሄደው 98ኛ መደበኛ ስብስበሰባው ላይ ነው።
ስትራቴጂው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስነ ምህዳሩን በማዘመን ውስን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ያለውና የፋይናንስ አካታችነቱ የጎለበተ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ፍኖተ ካርታ በመሆን የሚያገለግል ነው።
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ዲጂታል አሰራር በማሸጋገር የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ፣ የስራ እድል ለመፍጠርና የሴቶችን የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ ያገለግላል።
ከሀገር በቀል የሪፎርም ተግባራት ጋር በቅንጅት የሚፈጸመው ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ኢትዮጵያ ያስቀመጠችውን አካታች የኢኮኖሚ እድገት፣ የላቀ ብልጽግና እንዲሁም የተሻለ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ግብ ለማሳካት የሚያግዝ ነው።
የዲጂታል ክፍያ ረቂቅ ስትራቴጂው ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ስራ ላይ እንዲወል ወስኗል።