የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተመራማሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በሀገር አቀፍ ምርምር ጉዳዮች ላይ ምክክር አደርጓል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) ለሀገራዊ ምርምር ልማት አስፈላጊውን ትኩረትና ድጋፍ በመስጠት ዘላቂና ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ ተመራማሪውና ባለድርሻ አካላት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።
የሀገር በቀል ኢኮኖሚን ለማሻሻል የስራ ዕድል ፈጠራን በማጎልበት፣ የውጭ ገቢን በመጨመር፣ ሀገራዊ ምርትን በማሳደግና አዳዲስ ሀብት በመፍጠር ግስጋሴያችን ወደ አካታች ብልፅግና እንዲሆን የምርምር ስራው ላይ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል:ቴክኖሎጂዎችን በማልማት፣ በማሸጋገርና በመጠቀም፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ ለማቅረብ መንግስት አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
በቂ ዕውቀት፣ ክህሎትና አዎንታዊ አመለከከት ያለው የሰው ኃይል ያጎለበተ ዜጋና አመራር የማልማት ስራም ትኩረት ተሰጥቶታል ነው የተባለው። የዘርፉን የምርምርና ስርፀት ሥራዎች በመሰረታዊነትም ለመፍታት እና አቅም መገንባትን ታሳቢ ያደረገ ከ25 ሺህ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተገለፁዋል።
በምርምርና ስርፀት ዘርፍ የሰው ሀብት አቅም ግንባታን፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ሽግግርና የእዉቀት አስተዳደር ሥርዓትን፣ የምርምርና ልማት መሰረተ ልማትን፣ የምርምር ፋይናንስ አቅርቦት፣ ድጋፍና ማበረታቻን ፣ በምርምር ሥራ ትብብር እና ቅንጅትን እንደ ዋና የትኩረት መስኮች ናቸው።