የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶክተር በለጠ ሞላ የምክርቤቱን ምስረታ አስመልክቶ የተሰማቸውን ደስታ መልእክት ልከዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ሚኒስቴር መስሪያቢታቸው በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ስራንና ሀብትን ለመፍጠር የምትመች ሀገር ለመገንባት ርዕይን በመሰነቅ እየሰራ ነወ፡፡
በተለይ የዲጂታል ኢኮኖሚ የሚገነባበትን ከባቢያዊ ስርዓት ለመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ልማት ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችል አቅም እንዲገነባ እና ኢኖቬሽን፣ ቴክኖሎጂ እና ምርምር ለስራና ሀብት ፈጠራ አበርክቶ እንዲኖራቸው አልሞ እየሰራ ነው፡፡
ክቡር ሚኒሰትሩ በመልእክታቸው ሀገራዊ የኢኖቬሽን ስርአቱ ውጤታማ አንዲሆን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከክልሎች እና ከተማ መስተዳደሮች ጋር በትብብርና በቅንጅት ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ለአብነት ከሶማሌ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመቀናጀት Livestock Project እና Local Online Service ትግበራና የሳይንስ ካፌ ማቋቋም መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ተግባራት ዘርፍ ተሻጋሪ (Cross Sectoral) እንድመሆናቸው የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ይሻሉ፡፡
ዘርፉ ለጠቅላላ ሀገራዊ ምርት እድገት ያለውን አስተዋፅኦ የመምክር፣ የመገምገም እና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ዓላማ ያለው ብሔራዊ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ምክርቤት መኖሩን አውስተዋል፡፡
መሰል ምክር ቤቶች በሁሉም የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች እንዲቋቋሙ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያያደርግ ቢሆንም የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም ፋና ወጊ ሆኖ የምክር ቤቱ ምስረታ እንዲሳካ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቢሮ ሃላፊና የምክርቤቱ ሴክሪታሪያት ክብርት ወ/ሮ ፋጡማ መሐመድ በበኩላቸው ሚኒስቲር መስሪያቤቱ ክልሉን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለመደገፍ እያደረግ ላለው ጥረት አመስግነዋል፡፡
ዘርፉ የህዝቡ ኑሮ እንዲሻሻልና የክልሉ እምቅ አቅም በቴክኖሎጂ ታግዞ ለተጀመረው አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የድርሻውን እንዲያበረክት ያስችለዋል፡፡
የሶማሌ ብሄራዊ ክለላዊ መንግስት አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ለመቀበል ቀዳሚ ነው ያሉት ክብርት ፋጡማ የምክርቤቱ መቋቋም የክልሉን ህዝብ ጥረት ያግዛል ብለዋል፡፡
የፌደራል መንግስት ወቅቱን ያገናዝበና የክልሉን አሁናዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ድጋፎችን በሌሎች ዘርፎችም ጭምር ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
የፌደራሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክርቤት አሰራርና አደረጃጀትን የተመለከተ ገለጻም ለተሳታፊዎች ቀርቧል።